የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ የክረምት በጎ ፈቃደኞች ለችግረኛ ተማሪዎች ቃል የገቡትን የትምህርት ቁሳቁስ ለሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴው እያስረከቡ ይይገኛሉ።
በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ “አንድም ተማሪ በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ምክንያት ከትምህርት ገበታው መቅረት የለበትም” በማለት በጎ ፈቃደኞች ለችግረኛ ተማሪዎች ቃል የገቡትን የትምህርት ቁሳቁስ በወረዳው ለተዋቀረው የሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ እያስረከቡ ነው።
እስከ አሁን በኮሚቴው የተሰበሰቡ
1, ደብተር……… 84 ደርዘን
2, እስኪብርቶ…. 11 ፓኮ
3, ልብስ……….. 3 ሙሉ ቱታ እና 1 ጅንስ ኮት
4, ጫማ………… 3 ጥንድ
5, የደብተር መግዣ በአካውንት የተላከ 43,337 ብር /አርባ ሶስት ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ ሰባት ብር ብቻ/ ሲሆን
የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አብዮት ተራመደው ኮሚቴው ቁሳቁሱን በዚህ ልክ መሰብሰቡም ሆነ በፈቃደኝነት ለደገፉ በጎ አድራጊዎች ምስጋና አቅርበው ቃል ገብታችሁ እስካሁን ገቢ ያለደረጋችሁ አጋሮቻችን የትምህርት ጊዜው እየደረሰ ስለሆነ ቀድመን ለተማሪዎች ማድረስ እንድንችል ቃል የገባችሁትን በወቅቱ ገቢ እንድታደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን ብለዋል።
በጎነት ለማህበረሰብ ለውጥ