የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ
የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ በሰሜን ሸዋ ዞን ከሚገኙ 24 ወረዳዎች አንዱ ነው ወረዳው በዞኑ ውስጥ ከሚገኙ 5ቱ መንዞች ከሚባሉት አንዱ ነው ከዞኑ ርእሰ ከተማ ደ/ብርሃን 152 ኪሎ ሜትር ከአዲስ አበባ ደግሞ 282 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል
የወረዳው የቱሪስት መስህብ
1.የጓሳ ማህረሰብ ጥብቅ ሰፍራ ለ400 ዓመታት በህብረተሰቡ ሲጠበቅ የኖረው እና በውስጡ በርካታ አራዊት ቀይ ቀበሮ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ ነብር እና ሌሎችም ብርቅዬ አእዋፍና እንስሳት ያሉበት ቦታ በዓለም ላይ የሌሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የአእዋፍ ዝርያዎች 12% የሚሆኑት መገኛ ከተለያዩ የዓለም አገራት የሚመጡ ተመራማሪዎች ምርምር እያደረጉበት ያለ ቦታ ከሰሀረ በታች ካሉ የአፍሪካ አገራት ለ400 ዓመታት በህብረተሰቡ ብቻ በመጠበቁ ብቸኛ እና ልዩ የተባለለት ድንቅ ስፍራና አስደናቂ መልክአ ምድራዊ የተፈጥሮ አቀማመጥ ያለበት ቦታ፤ለ7 የአባይ ገባር ወንዞች የውሃ መነሻ የውሃ ቋት፤
2. በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተቆረቆረችው እና በውስጧ በርካታ ቅርሶችን የያዘችው በፌደራል ቅርስ ጥበቃ ባለስልጠን ጥገና የተደረገላት ፍርኩታ ኪዳነ-ምህረት ገዳም
3. የአፄ በእደ ማርያም ቤተ-መንግስት የነበረበት በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ተሠርቶ የነበረው ቤተ-መንግስት ፍርስራሽ እና በ1992ዓ/ም የፈረንሳይ አርኪዬሎጂስቶች ቦታው ላይ መጥተው ቁፋሮ አድርገው በርካታ ቅርሶች ተገኝተው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ይገኛሉ፡፡ በዚሁ ቦታ ጶጉሜ 3 በየዓመቱ ከሩፋኤል በዓል ጋር ተያይዞ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚውል ገቢያ አለ፡፡ በገቢያው ላይ የረከሰ እቃም ሆነ ሰብል ዓመቱን ሙሉ ይረክሳል የተወደደም ከሆነ ዓመቱን ሙሉ ይወዳዳል ተብሎ ይታመናል በሌላ አገላለጽ የዓመቱ ገቢያ የሚተነበይበት ነው፡፡
4. የመንዝ በግ በስጋው ጣፋጭነት እጅግ ተወዳጅ በመሆኑ የደ/ብርሃን ዩኒቨርስቲ መለያ ብራንድ ሰጥቶታል ይህ የመንዝ በግ በ5ቱም መንዞች የሚገኝ ነው ጦስኝ የሚባል ሣር እየተመገበ የሚያድግ በመሆኑ ስጋው ጣፋጭ ነው
5. የመንዝ ቅቤ በጣዕሙ እጅግ ተወዳጅ ሲሆን ተፈላጊነቱም እየጨመረ መጥቷል በቅርቡ መለያ ብራንድ ለመስጠት እንቅስቃሴ ተጀምሯል
6. አመድ ጉያ ሜዳ ለባለሀብቶች በእርሻ ስራ ኢንቨስት ማድረግና በሚፈልጉ ሰፊ እና የመብራት እና የመኪና መንገድ መሰረተ ልነማት የተሟላለት
መንዝ ጌራ ላይ እነዚህ እና ሌሎችም በርካታ ሃይማኖታዊ እና ተፈጥሮአዊ መስህቦች ያሉት ቦታ ነው አየሩ ለኑሮ ና ለጤና ተስማሚ የወረዳው መዲና የሆነችው መሐል ሜዳ በፈጣን እድገት ላይ የምትገኝ ሕዝቡ ስራ ወዳድ እና እንግዳ አክባሪ ነው በወረዳው እና መሐል ሜዳ ላይ በኢንቨስትመንት መሳተፍ ለምትፍልጉ ባለሀብቶች ፈጣን መስተንግዶ ለመስጠት ወረዳው ና ከተማ አስተዳደሩ ይጠብቋችኋል፡፤
የኢንቨስትመንት አማራጮች
ሆቴል እና ሎጅ
የማዕድን ውኃ
እርሻ
በግ እና ከብት እርባታና ማድለብ